ዝክረ ዓድዋ የስዕል አውደ ርእይ ተከፈተ

You are currently viewing ዝክረ ዓድዋ የስዕል አውደ ርእይ ተከፈተ

AMN- የካቲት 17/2018 ዓ.ም

በኮሪደር ልማት ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው የከተማዋ ቅርሶች መካከል አንዱ በሆነው እና ከተገነባ 117 ዓመታትን ባስቆጠረው በጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል ዝክረ ዓድዋ የስዕል አውደ ርእይ ተከፍቷል።

የስዕል ዐውደ ርእዩን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የማዕከሉ ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው ቅጣው ማዕከሉ በዚህ ደረጃ ቅርስነቱ እንዲጠበቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚመሰገን ስራ መስራቱ አውስተዋል።

ማዕከሉ ታሪክ የሚዘከርበትና ለትወልድ የሚተላለፍበት መሆኑንም ነው የገለፁት።

የህብር የስነ-ስዕል ማህበር የስዕል ስራዎቻቸውን በተለያዩ ቦታ ያቀርቡ እንደነበር ያነሳው ሰአሊ አለምሰገድ በሃይሉ ዛሬ ላይ ግን የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የጥንካሬ መገለጫ የሆነውን የአድዋ ድል በዓልን በማስመልከት ድሉን የሚዘክሩ ስራዎች ማቅረባቸውን ነው የገለፀው።

በዝክረ ዓድዋ የስዕል ኤግዚብሽን ደራሲ ዘነበ ወላን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው ታዳሚዎች ተገኝተዋል።

130ኛው የአድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የስዕል ኤግዚብሽን እስከ መጋቢት 17/2018 ዓ.ም ሁሉም ዜጋ በነፃ እንዲጐበኘው ክፍት የተደረገ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

በያለው ጌታነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review