AMN-የካቲት 17/2019
የአዲስ አበባ ባህል፣ኪነ ጥበብ ቢሮ 130ኛውን የአድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ “የአድዋ ትሩፋት በጥበብ አንደበት” በሚል መሪ ቃል እያከበረ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሉባባ ጀማል፣አባትና እናት አርበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ወቅቱን የሚያስታውሱ የተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ስራዎች ለታዳሚያን እየቀረቡ ይገኛል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት በቢሮው የኪነ ጥበብ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሉባባ ጀማል አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል ብቻም ሳይሆን የይቻል መንፈስን ያሳደገ እንደሆነ ገልፀዋል።
የአድዋ ድል የግዛት ሉአላዊነት ያረጋገጠ ብቻ ሳይሆን፣በአንድነት ከተባበርንና ከሰራን ውጤቱ ድል እንደሚሆንም ያሳየ ነው ብለዋል።
አድዋ በድፕሎማሲ ረገድ የሰጠው ትምህርት ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ረገድ እያስመዘገበቻቸው ያሉ ስኬቶች ማሳያም ጭምር መሆኑን አንስተዋል።
እንደ ሀገር ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል ወደ ኢኮኖሚ ሉዓላዊነት የሚያሸጋግሩ ሰፋፊ ስራዎች እየሰሩ መሆናቸውንም እንስዋል።
በሚካኤል ሂሩይ