ለዜጎች አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ

You are currently viewing ለዜጎች አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ

AMN- የካቲት 19/2018 ዓ.ም

ለዜጎች አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ የማዘመንና ተደራሽ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈፃፀሙን እየገመገመ ይገኛል።

ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ፣ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገድ፣ የኤሌክትሪክ መብራት እና የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ተቋማት ባለፉት ስድስት ወራት በአገልግሎት አሰጣጥ ዜጎችን በማስደሰት ረገድ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።

በዚህም አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ መደገፍ፣ የአደረጃጀት፣ የሰው ሃብት ልማትና ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም የዜጎችን አገልግሎት አሰጣጥ የማሻሻል፣ የማዘመንና ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናግረዋል።

የሥራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት የሁሉም ተቋማት የስድስት ወራት የሥራ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review