ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከፕሬዝዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከፕሬዝዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያዩ

AMN መጋቢት 4/2018

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከፕሬዝዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር መወያየታቸዉን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ የጸና ወዳጅነት፣ በመተማመን ላይ የተመሠረተ ትብብር! ሲሉ

ባሰፈሩት መልዕክት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በነበረኝ የስራ ጉብኝት ከፕሬዝዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተገናኝቼ ተወያይተናል ብለዋል።

‎ውይይታችን በኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ለረጅም ዘመናት የቆየውን ወዳጅነት በማጎልበት፤ ትብብር እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር።

ለተደረገልኝ አቀባበል እና በሀገሮቻችን መካከል የፀና ወዳጅነታችንን የበለጠ ለማጠናከር ለተጋራነው የፀና አቋም ምስጋናዬ የላቀ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review