AMN-መጋቢት 6/2018 ዓ.ም
ማንችስተር ዩናይትድ በ30ኛ ሳምንት የሊግ መርሐግብሩ በኦልድትራፎርድ አስቶንቪላን አስተናግዶ 3ለ1 አሸንፏል።
ካሲሜሮ ፣ ማቴኡስ ኩኝሃ እና ቤንጃሚን ሼሽኮ የዩናይትድን ሦስት ግቦች ማስቆጠር ችለዋል።
ቡርኖ ፈርናንዴዝ ከሦስቱ ግቦች ሁለቱን አመቻችቶ አቀብሏል። ፖርቹጋላዊው አማካይ በአጠቃላይ በውድድር ዓመቱ 16 ግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቷል።
ይህም በዩናይትድ አዲስ ታሪክ ሲሆን ፣ በፕሪምየር ሊጉ ቴሪ ኦንሪ እና ኬቨን ደብሩየና የሰሩትን ታሪክ ለመድገም አራት አመቻችቶ ማቀበል ይኖርበታል።

ተከታታይ ጨዋታ ለተሸነፈው ቪላ ብቸኛውን ግብ ሮስ ባርክሌይ ማስቆጠር ችሏል።
ድሉን ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ ነጥቡን 54 አድርሷል። አስቶንቪላ ደግሞ 51 ነጥብ አለው።
በሌሎች ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ ከሊድስ ዩናይትድ ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከፉልሃም በተመሳሳይ 0ለ0 ተለያይተዋል።
በሸዋንግዛው ግርማ