የዶናልድ ትረምፕ ፊርማ በአሜሪካ የወረቀት ገንዘብ ላይ ሊካተት ነው

You are currently viewing የዶናልድ ትረምፕ ፊርማ በአሜሪካ የወረቀት ገንዘብ ላይ ሊካተት ነው

AMN- መጋቢት 18 /2018ዓ.ም

በአሜሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ፊርማ የአሜሪካ የወረቀት ገንዘብ ላይ ታትሞ በመጪው ሰኔ ለአገልግሎት እንደሚውል የሐገሪቱ ግምጃ ቤት አስታወቀ።

ፊርማቸውን በአሜሪካ ገንዘብ ላይ በማሳረፍ በታሪክ በስልጣን ላይ ያሉ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ያደርጋቸዋል።

እንደገና የተቀረፁት የገንዘብ ኖቶች የአሜሪካን 250ኛ ዓመት የነፃነት በዓል ለመዘከር የታሰቡ መሆናቸው ነው የተገለፀው።

የዶናልድ ትረምፕ ፊርማ ያለበት የመጀመሪያው የመቶ ዶላር ገንዘብ በመጪው ሰኔ እንደሚታተም እና የሌሎቹ የገንዘብ ኖቶች ሕትመት በተከታታይ ወራት እንደሚከናወን ፍራንስ 24 ዘግቧል።

ዶናልድ ትረምፕ በአሜሪካ ሳንቲሞች ላይ ምስላቸውን ለማስፈር ጥረት እያደረጉ ቢሆንም የአሜሪካ ሕግ በስልጣን ላይ ያለ ፕሬዝዳንት ምስል እንዳይታተም ስለሚከለክል ከፍተኛ ትችት ተሰንዝሮባቸዋል።

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review