AMN- መጋቢት 24/2018 ዓ.ም
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስተዳደርና ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለተመዘገቡ ስኬቶች ያላቸውን ድጋፍ በሰልፍና በማስ ስፖርት ገልፀዋል።
የድጋፍ ሰልፉ በአገሪቱ እየተመዘገበ ያለውን የለውጥ ጉዞ የሚያደንቁ ሃሳቦች በተንፀባረቁበት እና በኢትዮጵያ እንዲሁም በመዲናዋ እየተመዘገበ ላለው ፈጣን የልማት ስራ ዕውቅና ተሰጥቶታል።
ሰልፈኞቹ ይዘዋቸው በወጡትና እያሰሟቸው ባሉ የድጋፍ ድምጾች “መጋቢት 24 የኢትዮጵያ ከተሞች ትንሳኤ የጀመረበት” እለት ነው ብለዋል።
በመዲናዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል ዝግጁነታቸውን ያረጋገጡት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የድጋፍ ሰልፈኞች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ልዩ ምስጋናችን” ይድረስ ብለዋል።
ካሳሁን አንዱዓለም