ከአዘዞ ጀምሮ እስከ ፒያሳ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ ጎንደር ዳግም ለመወለድ እያማጠች እንደሆነ ያሳያል። ይህ ምጥ ሙያተኛ ይፈልጋል፤ ሐኪም ይፈልጋል። አሁን ባለበት ከቀረ ይጨነግፋል፤ አይወለድም። ደግፈን አግዘን እንዲወለድ ካደረግነው ግን ልክ በፋሲል ቅጥር ግቢ እንደሚታየው ያለ ውበት በመላ ጎንደር ከተማ ውስጥ ሊታይ ይችላል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የታደሰውን የፋሲል ጊቢ መርቀዋል። የተከናወነው ሰፊ የእድሳት ሥራ በቅርስ ስፍራው ነባሩን ታሪክ በመጠበቅ ውበቱን እና ተደራሽነቱን በማሻሻል አዲስ እስትንፋስ የሰጠ ሆኗል።