ከአዘዞ ጀምሮ እስከ ፒያሳ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ ጎንደር ዳግም ለመወለድ እያማጠች እንደሆነ ያሳያል። ይህ ምጥ ሙያተኛ ይፈልጋል፤ ሐኪም ይፈልጋል። አሁን ባለበት ከቀረ ይጨነግፋል፤ አይወለድም። ደግፈን አግዘን እንዲወለድ ካደረግነው ግን ልክ በፋሲል ቅጥር ግቢ እንደሚታየው ያለ ውበት በመላ ጎንደር ከተማ ውስጥ ሊታይ ይችላል።