20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በውቢቱ ሆሳዕና ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበዓሉ ባደረጉት ንግግር “የኢትዮጵያን ችግሮች ብቻ ሳይሆን አቅሞቿን መመልከት ይገባናል” ብለዋል።