
AMN-ታህሣሥ 15/2017 ዓ.ም
በኦሮሚያ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እና በቅርቡ ከመንግስት ጋር ስምምነት የፈፀሙ ግለሰቦች የተሳተፉበት የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ተጠናቋል።
ተሳታፊዎች ያለምንም ገደብ በነፃነት ለሀገር ሰላምና አንድነት መሰረት የሆኑ አጀንዳዎችን ስለማንሳታቸው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ተናግረዋል።
የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሃግብሩ በርካታ ሰዎች በአንድ መድረክ ተገኝተው የመከሩበት ግዙፍና ስኬታማ መድረክ ነበር ያሉት ዋና ኮሚሽነሩ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት በምክክሩ መሳተፋቸውም ታላቅ ስኬት መሆኑን አብራርተዋል።
በካሳሁን አንዱዓለም