ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን ከ7 መቶ ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ደርሷል – የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

You are currently viewing ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን ከ7 መቶ ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ደርሷል – የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም

ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን ከ7 መቶ ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን 2.4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ከተያዘው እቅድ ውስጥ እስከ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ 700 ሺህ 763.2 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

ጅቡቲ ወደብ ከደረሰው 700 ሺህ 763.2 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 658 ሺህ 249.2 ሜትረክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ የተጓጓዘ ሲሆን፣ ቀሪው 42ሺህ 513.9 ሜትሪክ ቶን ደግሞ በወደብ እንደሚገኝ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review