20ኛው የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በቡሌ ሆራ ከተማ እየተከበረ ነው

You are currently viewing 20ኛው የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በቡሌ ሆራ ከተማ እየተከበረ ነው

AMN ህዳር 22/2018

በኦሮሚያ ክልል ደረጃ 20ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በቡሌሆራ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡

በበዓሉ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ፣የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱራህማንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች ታድመዋል።

ቀኑ በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ትዕይንት፣ በማርሽ ባንድና በህጻናት ትርዒቶች በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በድምቀት እየተከበረ ነው።

በዓሉ “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኀብረብሄራዊ አንድነት” በሚል ርዕስ በየደረጃው በተለያዩ ዝግጅቶች በክልሉ ሲከበር ቆይቶ ዛሬ የማጠቃለያ መርሃ ግብር መሆኑም ታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review