በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፓሪሰን ዠርማ እና ሪያል ማድሪድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸኘፉ

AMN-ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ፓሪሰን ዠርማ እና ሪያል ማድሪድ ድል ቀንቷቸዋል።

በኢትሃድ ስታዲየም ፓሪሰን ዠርማን ያስተናገደው ማንቸስተር ሲቲ 4ለ2 ተሸንፏል። ዴዚሪ ዱዌ ፣ ኡስማን ዴምቤሌ ፣ ቪቲንሃ እና ማህነስ አክሊኡች የፈረንሳዩን ክለብ የማሸነፊያ ግቦች አስገኝተዋል።

ኧርሊንግ ሃላንድ ሁለቱንም ግቦች ለሲቲ አስቆጥሯል። ጨዋታውን የቀድሞ የሲቲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ኢትሃድ በመገኘት ተመልክቶታል።

በሌላ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ በእጅጉ ተፈትኖ ሮማን 4ለ3 አሸንፏል። ኪሊያን ምባፔ ፣ ካርሎስ ኤስፒ ፣ ኤንድሪክ እና አንቶኒዮ ሩዲገር የስፔኑን ክለብ የማሸነፊያ አራት ግቦች ያስቆጠሩ ናቸው።

ለሮማ ዶኒየል ማለን ሁለት እንዲሁም ማርቲን ደሩን ሌላኛውን ግብ አስቆጥረዋል። በጨዋታው የሮማ ደጋፊዎች ለቀድሞ አሰልጣኛቸው ጆዜ ሞሪንሆ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።

በሌሎች ጨዋታዎች አስቶን ቪላ ፌነርባቼን 6ለ0 ሲረታ ፣ ቦዶ ቦሩሲያ ዶርትመንድን 1ለ0 አሸንፏል።

ሪያል ቤቲስ ፖርቶን 3ለ2 በማሸነፍ ተከታታይ ድል ሲያስመዘግብ ፣ ስቱትጋርት ስሎቫን ብራቲስላቭን 3ለ0 አሸንፏል። ሻካታር ዶኔትስክም አኢኬ አቴንስን 3ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review