ኢትዮጵያ የአፍሪካን ቴክኖሎጂ ለመምራት ትሰራለች- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing ኢትዮጵያ የአፍሪካን ቴክኖሎጂ ለመምራት ትሰራለች- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN – መስከረም 28/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የአፍሪካን ቴክኖሎጂ ለመምራት እንደምትሰራ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ኮንፍረንስ ፓን አፍሪኮን ኤ.አይ 2024 በአዲስ አበባ መካሄድ እየተካሄደ ነው።

በዓድዋ ድል መታሰቢያ ለሁለት ቀናት የሚካሄደው ኮንፍረንስ “አፍሪካን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማላቅ” በሚል መሪ ሀሳብ ነዉ እየተካሄደ የሚገኘው።

በመድረኩ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና በርካታ ከፍተኛ ሚኒስትሮችና የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አፍሪካ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን ሳትችል እንደቆየች ጠቅሰው ኢትዮጵያ የአፍሪካን ቴክኖሎጂ ለመምራት ትሰራለች ብለዋል።

ፓን አፍሪኮን አፍሪካ የቴክኖሎጂ ውጥኖችን በመቅረጽ ረገድ ያላት ሚና እያደገ መምጣቱን አመላካች መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ዘርፉ በሁሉም እንቅስቃሴዎች ውስጥ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህንን መሰረት በማድረግ ኢትዮጵያ ከዘርፉ የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራች ነው ብለዋል፡፡

ኮንፍረንሱ ለሶስተኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለ ሲሆን የዘርፉ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉበት ይገኛሉ።

በሃብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review