የዓለም የቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን ዓመታዊ ጉባዔ በሆንግ ኮንግ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing የዓለም የቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን ዓመታዊ ጉባዔ በሆንግ ኮንግ እየተካሄደ ነው

AMN – ሚያዝያ 07/2017

አዲስ አበባ ከተማ አባል የሆነችበት የዓለም የቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን (WTCF) የ2025 ዓመታዊ ጉባዔ ”Innovative City Branding Elevates Tourism Excellence Time” በሚል መሪ ቃል በቻይና ሆንግ ኮንግ እየተካሄደ ነው።

የአባል ከተሞች ከንቲባዎች እና የዘርፉ ሀላፊዎች የታደሙ ሲሆን፤ በጉባዔው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና ዶክተር ሂሩት ካሳው የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ እየተሳተፉ ነው።

በዛሬው ጉባዔ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በተገኙበት የሀረር ከተማ በአባልነት ፌዴሬሽኑን በይፋ ተቀላቅላለች።

በአባል ከተሞች የከንቲባዎች ፎረም መክፈቻ ላይ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና አቶ ኦርዲን በድሪ በምስል የተደገፈ ንግግር በማድረግ ሁለቱን ከተሞች በጉባዔው ለተሳተፉ ከንቲባዎች አስተዋውቀዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review