ከደረሰኝ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ የ20 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበሉ ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

You are currently viewing ከደረሰኝ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ የ20 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበሉ ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

AMN – የካቲት 14/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የደረሰኝ ቁጥጥር ባለሙያዎች ባልተገባ ሁኔታ በደረሰኝ ቁጥጥር ስም የ20 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበሉ ግብር ከፋዩ ባደረሰው ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ጉቦውን ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ የተያዙት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 መርካቶ አካባቢ ከሚገኝ ሆቴል ውስጥ መሆኑን ከአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ብልሹ አሰራሮችንና የሌብነት ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያደርገው ጥረት ላይ የህብረተሰቡ ተሳትፎ እየጨመረ በመምጣቱ የሚያስመሰግን መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም 7075 ነፃ መስመርን በመጠቀም ጥቆማ በማድረስ ትብብሩን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review