በካናዳ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት

You are currently viewing በካናዳ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት

AMN-ግንቦት 24/2017 ዓ.ም

በካናዳ ማኒቶባ ክፍለ ሃገር የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት በፍጥነት በመዛመት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

የህይወት አድን ሰራተኞች የጦር አውሮፕላኖችን እና ሄሊኮፕተሮች በመጠቀም ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማሸሽ ላይ ይገኛሉ።

በምዕራብ ካናዳ ሳስካችዋን እና ማኒቶባ አካባቢዎች እስካሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መኖሪያቸውን ለቅቀው እንዲወጡ መደረጉም ታውቋል።

በአካባቢዎቹ ለአንድ ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን የአካባቢው ባለስልጣናትም ተጨማሪ የእሳት አጥፊ ባለሙያዎች ላኩልን ጥሪ ለዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ ማስተላለፉቸው ተነግሯል።

በአካባቢዎቹ በቀጣይ ቀናት ደረቅ እና ሞቃታማ የዓየር ንብረት እንደሚኖር መተንበዩን ተከትሎ ሰደድ እሳቱን የመቆጣጠር ሥራው ይቀልጥ ፈታኝ እንዳይሆን መሰጋቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

በእዮብ መንግሥቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review