ኤ ኤም ኤን ላበረከተው የላቀ የዘገባ አስተዋፅዖ እውቅና አገኘ

You are currently viewing ኤ ኤም ኤን ላበረከተው የላቀ የዘገባ አስተዋፅዖ እውቅና አገኘ

AMN-ግንቦት 27/2017 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ኢትዮጵያ ባስተናገደችው 20ኛው የአለም ስራ ድርጅት (ILO) ጉባኤ ላይ ባበረከተው የላቀ አጋርነት እና የዘገባ ድርሻ ዕውቅና አገግኝቷል።

ዕውቅናውን የአዲስሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ከከተማና መሰረተልማት ሚንስትሯ ጫልቱ ሳኒ እጅ ተቀብለዋል።

የከተማና መሰረተልማት ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ መንገዶች አሰተዳደር በጋራ ባመቻቹት በ20ኛው የዓለም የስራ ድርጅት ጉባኤ ኢትዮጵያ በሁሉም መመዘኛዎች ከሀያዎቹ ጉባኤዎች ሁሉ በተሻለ ሁኔታ ማዘጋጀቷ ተገልጿል።

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ኮንፈረንሱ የተካሄደባት የአዲስአበባ ከተማ ሚዲያ እንደመሆኑ ሁነቱን በሚመጥን መንገድ ሰፊ የሚዲያ ሸፋን በመስጠቱ ዕውቅናውን ስለማግኘቱም ተገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review