በፓኪስታን የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 699 ደረሰ

You are currently viewing በፓኪስታን የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 699 ደረሰ

AMN – ነሐሴ 13/2017 ዓ.ም

በፓኪስታን በቀጠለው ጎርፍ ያስከተለ ከባድ ዝናብ ባለፉት 24 ሰዓታት የ26 ሰዎች ህይወት በማለፉ የሟቾች ቁጥር 699 መድረሱ ተዘግቧል፡፡

የሃገሪቱ ብሔራዊ እና የክልል የአደጋ አስተዳደር ባለስልጣናት እንደገለፁት ከሆነ ሰኞ እለት በቀጠለው ከባድ ዝናብ በሃገሪቱ የተለያዩ ከተሞች የ26 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ብዙዎች ያሉበት አልታወቀም፡፡

በፓኪስታን ቡነር ከተማ የምትገኝ ቤሾናይ መንደር አብዛኛው ክፍል በጎርፍ ተጠርጎ የተወሰደ ሲሆን፤ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እስካሁንም የተረፉ ሰዎችን በማፈላለግ ላይ እንደሚገኙ አናዶሉ ዘግቧል፡፡

በሃገሪቱ አንዳንድ ክልሎች ከባድ ዝናብ እስከ ነሐሴ 21 ድረስ ሊቀጥል እንደሚችል ባለስልጣናቱ አስጠንቅቀዋል፡፡

የሃገሪቱ የመረጃ እና ብሮድካስቲንግ ሚኒስትር አታኡላ ታራር እንዳስታወቁት ከሆነ አደጋው ከደረሰባቸው አካባቢዎች ከ25 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ሲፈናቀሉ፤ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች በሆስፒታሎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review