ዌስትሃም ዩናይትድ እና ቼልሲ የሊጉን ሁለተኛ ሳምንት መርሃግብር ይጀምራሉ

You are currently viewing ዌስትሃም ዩናይትድ እና ቼልሲ የሊጉን ሁለተኛ ሳምንት መርሃግብር ይጀምራሉ

AMN – ነሃሴ 16/2017 ዓ.ም

በመጀመሪያ ሳምንት ነጥብ የጣሉት ዌስትሃም እና ቼልሲ በለንደን ኦሊምፒክ ስታዲየም የሊጉ የሁለተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ያከናውናሉ፡፡

በመጀመሪያ ሳምንት መርሃግብር ቼልሲ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ከክሪስታል ፓላስ ጋር 0ለ0 ሲለያይ ፤ ዌስትሃም ዩናይትድ በአዲስ አዳጊው ሰንደርላንድ 3ለ0 ተረቷል፡፡

የቀድሞ ክለባቸው ቼልሲን ለመግጠም የተዘጋጁት ግራሃም ፖተር በዝውውር መስኮቱ የተሳካ ጊዜ እያሳለፉ አይገኙም፡፡ ኮከብ ተጫዋቹ ሞሃመድ ኩዱስን ያጣው ዌስትሃም አምስት ተጫዋቾችን ቢያስፈርምም ደጋፊዎችን አላስደሰተም፡፡

ዌስትሃም ዩናይትድ ከቼልሲ ጋር ያለው ክብረወሰን ደካማ የሚባል ነው፡፡ ቼልሲ በፕሪምየር ሊጉ የዛሬ ተጋጣሚውን 32 ጊዜ አሸንፏል፡፡

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ በሊጉ ታሪክ ከቶትንሃም(37) በመቀጠል ብዙ ጊዜ ያሸነፈው ዌስትሃምን እንደሆነ የኦፕታ ቁጥራዊ መረጃ ያሳያል፡፡

ቼልሲን ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲያደርጉ የሚጠበቅባቸው ኢንዞ ማሬስካ አሁንም ተጫዋቾች እንዲፈርሙላቸው ይፈልጋሉ፡፡

ክለቡ ዘጠኝ ተጫዋቾችን ቢያስፈርምም ጣልያናዊው አሰልጣኝ ግን በተለይ ከግራ እየተነሳ የሚያጠቃ እና ተከላካይ እንዲፈርምላቸው ጠይቀዋል፡፡

የክለቡ ሃላፊዎች ግን በተለይ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች የማስፈረም እቅድ እንደሌላቸው እየተነገረ ይገኛል፡፡

ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review