ማንችስተር ዩናይትድ በአስደንጋጭ ሽንፈት ከካራባኦ ካፕ ውጪ ሆነ

You are currently viewing ማንችስተር ዩናይትድ በአስደንጋጭ ሽንፈት ከካራባኦ ካፕ ውጪ ሆነ

AMN – ነሃሴ 21/2017 ዓ.ም

ማንችስተር ዩናይትድ በእንግሊዝ አራተኛ የሊግ እርከን (ሊግ 2) በሚወዳደረው ግሪምስቢ ታውን በመለያ ምት ተሸንፎ ከካራባኦ ካፕ ውድድር ውጪ ሆኗል።

ጨዋታው 2ለ2 ሲጠናቀቅ ለዩናይትድ ብሪያን ምቤሞ እና ሀሪ ማጓየር ሲያስቆጥሩ ለግሪምስቢ ታውን ቻርለስ ቬርናም እና ታይረል ዋረን ሁለቱን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

ጨዋታው ቀጥታ ወደ መለያ ምት ሲያመራ ግሪምስቢ 12ለ11 አሸንፏል።

በዩናይትድ በኩል ማቴኡስ ኩኝሃ እና ሁለተኛ መለያ ምት የመታው ብሪያን ምቤሞ ስተዋል።

ሩበን አሞሪም አሉኝ የሚላቸውን ተጫዋቾች በሙሉ ቢጠቀምም አራት ሚሊየን ዩሮ ብቻ በሚገመተው የግሪምስቢ ታውን ስብስብ ተሸንፏል።

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ በውድድር ዓመቱ ሦስት ጨዋታ ብቻ ቢያደርግም ገና ካሁኑ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብቷል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review