የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ለኢትዮጵያ ሰላምና ህብረ ብሔራዊ አንድነት መጎልበት በቅንነት የለፉ አባት ነበሩ

You are currently viewing የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ለኢትዮጵያ ሰላምና ህብረ ብሔራዊ አንድነት መጎልበት በቅንነት የለፉ አባት ነበሩ

AMN- ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም

የቀድሞ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ ለኢትዮጵያ ሰላምና ህብረ ብሔራዊ አንድነት መጎልበት በቅንነት የለፉ አባት መሆናቸውን የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ገለጹ፡፡

የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስክሬን ሽኝት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡

በሥነ-ስርዓቱ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ፣ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በአመራር ዘመናቸው የሙስሊም ማህበረሰብን አንድነት እንዲጠናከር በተለይም ተቋሙ እውቅና አግኝቶ እንዲቋቋም ባደረጉት በጎ አስተዋፅዖ ይታወሳሉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ለኢትዮጵያ ሰላምና ህብረ ብሔራዊ አንድነት መጎልበት በቅንነት የለፉ አባት መሆናቸውንም አንስተው ይህ በጎ ተግባራቸውም ሁሌም የሚዘከር እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ለቤተሰባቸው፣ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review