አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና የዲፕሎማቶች መነኃርያ እንደመሆንዋ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ ውብ ፅዱና ማራኪ እንዲሁም የቱሪዝም መዳረሻ ተወዳዳሪ ለማድረግ ደረጃዋን የጠበቀች ውብ ከተማ በመገንባት ሂደት በኮሪደር ልማት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ::
የኮሪደር ልማቱ ካስገኛቸው ትሩፋቶች መካከል ዘመናዊ የንግድ ቤቶች በዋናነት ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው፡፡
በኮሪደር ልማቱ ብቻ 5200 የንግድ ሱቆች እና ፕላዛዎች በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ተገንብተዋል ፡፡ ከነዚህም ውስጥ 4972 ለተጠቃሚዎች ተላልፈው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ::
የተሟላ ብልጽግናን ለማረጋገጥና ከከተሜነት እድገት ጋር የተሳሰረው የኮሪደር ልማት ያስገኛቸው እነዚህ ንግድ ቤቶች እና ፕላዛዎች ከዚህ ቀደም ለመገልገልም ሆነ ለእይታ ምቹ ያልነበሩ ያረጁ ንግድ ቤቶች ተነስተው በምትካቸው የአካባቢውን ውበት በቀየሩ እና እይታን በሚስቡ ዘመናዊ ሱቆች እና ፕላዛዎች በመተካታቸው ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀት ከመሆን ባለፈ በዋናነት የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው::
እነዚህ የንግድ ሱቆቹ የከተማዋን ኢኮኖሚ በማነቃቃት ፤ የኑሮ ውድነትን በመቅነስ እና ገበያውን በማረጋጋት ረገድም የጎላ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡
ቀሪዎቹ 228 ሱቆችም በቀጣይ ጥቂት ቀናት ወደ ስራ የሚገቡ መሆኑን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።