ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሦስት አዳዲስ ሆስፒታሎች አጠቃላይ የግንባታ ሂደትን መገምገማቸዉን ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሦስት አዳዲስ ሆስፒታሎች አጠቃላይ የግንባታ ሂደትን መገምገማቸዉን ገለጹ

AMN ህዳር 12/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ ማለዳ ለህዝባችን ጥያቄ ተጨባጭ ምላሽ እየሰጠንባቸዉ ካሉት ስራዎች አንዱ የሆነዉን የሦስት አዳዲስ ሆስፒታሎች አጠቃላይ የግንባታ ሂደት ገምግመናል ብለዋል፡፡

ሆስፒታሎቹ ከነበሩን ሆስፒታሎች የተሻለ/የላቀ አገልግሎት የሚሰጡ ሆነዉ እየተገነቡ ያሉ ሲሆን ግንባታቸዉም በመጠናቀቅ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ሆስፒታሎቹን እገነባን ያለነዉ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች ነዉ።

ሆስፒታሎቹ ከዚህ ቀደም ሆስፒታል ባልነበረባቸዉ አካባቢዎች መገንባታቸዉ የህክምና ፍትሀዊ ተደራሽነትን ከማስፋታቸዉ በተጨማሪ ከመላዉ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናል።

አጠቃላይ 1,500 አልጋ የሚኖራቸዉ ሲሆን ፣ አሁን ላይ ግንባታቸዉ እየተጠናቀቀ ነዉ ፣ ቀጣዩ ትኩረታችን ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን ማስገባት ነው።

አዳዲሶቹ ሆስፒታሎች ለህዝባችን ጥያቄ ተጨባጭ ምላሽ ከመስጠት ባሻገር በሚሰጡት ዘመናዊ የህክምና አገልግሎት የልህቀት ማዕከል ሆነው የሚያገለግሉ ሲሆን፣ ከተማችንን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተያዘዉን ግብ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩ ይሆናል።

አስተዳደራችን ከአዲስ ሆስፒታሎች ግንባታ በተጨማሪ በሚኒሊክ፣ በራስ ደስታ እና በዘዉዲቱ ሆስፒታል አዲስ ሆስፒታል የመገንባት ያህል የማስፋፊያ ስራ ገንብተናል። ከእነዚህም ውስጥ የዘዉዲቱ ሆስፒታል ማስፋፊያ ተጠናቅቆ ስራ ጀምሯል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review