አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ‘ዉብ አዲስ’ የተሰኘ በአይነቱ አዲስ የሆነ ተከታታይ የቤተሰብ ድራማ በቅርቡ ሊጀምር ነዉ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ‘ዉብ አዲስ’ የተሰኘ በአይነቱ አዲስ የሆነ ተከታታይ የቤተሰብ ድራማ በቅርቡ ሊጀምር ነዉ

AMN ታኅሣሥ 7/2018

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ‘ዉብ አዲስ’ የተሰኘ በአይነቱ አዲስ የሆነው ተከታታይ የቤተሰብ ድራማ በቅርቡ እንደሚጀምር አስታወቀ።

ኤኤምኤን ተከታታይ የቤተሰብ ድራማዉን በቅርቡ መጀመር የሚያስችለዉን የፊርማ ሥነስርዓት በአራዳ ፓርክ አካሂዷል።

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ እና የፊልሙ ጸሐፊና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ተሾመ የፊርማ ሥነ ሥርዓቱን አከናዉነዋል።

‘ውብ አዲስ’ ድራማ በይዘትም በአቀራረብም ለየት በማለት በቅድሚያ የትወና ታለንት ውድድር በማድረግ ወጣት ተዋንያንን ከአንጋፋዎቹ ጋር አዋሕዶ የሚሠራ ተከታታይ ድራማ መሆኑ ተገልጿል።

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኤኤምኤን የማኔጅመት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በኤፍሬም ገ/መስቀል

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review