የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ለብሔራዊ ቡድን ዝግጅት መጠቀም አለብን- አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር)

You are currently viewing የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ለብሔራዊ ቡድን ዝግጅት መጠቀም አለብን- አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር)

AMN- ታኅሣሥ 15/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በአንጎላ ሉዋንዳ የተደረገው 4ኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ ውድድር ተሳትፎ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

በማሪዮት ሆቴል በተከናወነው መግለጫ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ ስራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዋል።

በሰባት የስፖርት ዓይነቶች የተካፈለችው ኢትዮጵያ ያመጣችው 33 ሜዳልያ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ተነስቷል። ከተካፈለችባቸው የስፖርት ዓይነቶች በአራቱ ሜዳልያ ማምጣት መቻሉ አበረታች እንደሆነ ተገልጿል። በተለይ ከዚህ ቀደም ሜዳልያ ባልተገኘበት ክብደት ማንሳት ውጤት መመዝገቡ በቀጣይ ጠንክሮ ለመስራት መነሻ እንደሚሆን በመግለጫው ተወስቷል።

በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ከወዲሁ ዝግጅት መጀመር እንደሚገባ ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ተናግረዋል። ለዚህም በውድድሩ የተሳተፉ የብሔራዊ ቡድን ስፖርተኞች መበተን የለባቸውም ብለዋል።

በዋነኛነት የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ለብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በ2027 የሚከናወነው 5ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ እንድታዘጋጅ መመረጧም ትልቅ ስኬት እንደሆነ ተነግሯል።

ዶክተር አሸብር የተጣለብንን እምነት ለመካስ እና ኢትዮጵያ ታላቅነቷን እንድታሳይ ከአሁኑ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። ያማረ ውድድር ለማሰናዳት የሚመለከተው ሁሉ ሊያግዝ ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review