አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የህዝብ ቅሬታዎችን በማሰማት እና እንዲፈታ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና መጫወቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የህዝብ ቅሬታዎችን በማሰማት እና እንዲፈታ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና መጫወቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN-ጥር 29/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የህዝብን ድምፅ በማሰማት እና የመንግስትን የአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል ረገድ ቁልፍ ሚና እየተወጣ መሆኑን ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች ይህንን የገለጹት የከተማዋ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የ6 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው።

ባለፉት ስድስት ወራት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በተከናወኑ ተግባራት ተገልጋዮች በቀጥታ ተሳትፎ እንዲያደርጉና አመራሩም ተጠያቂነትን እንዲያሰፍን የሚያስችል ስርዓት ተዘርግቷል።

ለዚህም በተቋሙ የሚመሩት እንደ “አገልጋዩ”፣ “ዋርካ” እና የምርመራ ጋዜጠኝነት ያሉ የሚዲያ መድረኮች ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።

በተለይም በ“አገልጋዩ” የቴሌቪዥን ፕሮግራም አማካኝነት የተቋም አመራሮች የህዝቡን ቅሬታ በቀጥታ ስርጭት እንዲያዳምጡና ወዲያውኑ መፍትሄ እንዲሰጡ መደረጉን ከንቲባዋ ጠቁመዋል። በዚህም ሂደት፡-

* በሚዲያ ከተነሱ የተገልጋይ ጥያቄዎች መካከል 86 በመቶ የሚሆኑት እውነተኛ ችግሮች መሆናቸው ተረጋግጧል።

* እነዚህ ችግሮች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መፈታታቸውን በመንግስት በኩል በተደረገ የመስክ ምልከታ ማረጋገጥ መቻሉንም ከንቲባ አዳነች ጠቅሰዋል። ይህ በሚዲያ የታገዘ አሰራር መንግስት የህዝብን ጥያቄዎች ለቅሞ እንዲፈታ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አረጋግጠዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review