የ2026 ምርጥ ተጫዋች ማን ይሆናል?

You are currently viewing የ2026 ምርጥ ተጫዋች ማን ይሆናል?

AMN-ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም

የእንግሊዝ እግርኳስ ተጫዋቾች ማኅበር (PFA) በተለያየ ዘርፍ እጩ አድርጎ የመረጣቸውን ተጫዋቾች አሸናፊ ዛሬ ይፋ ይደረጋል።

ዘንድሮ ለ53ኛ ጊዜ በሚከናወነው በዚህ የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ በተለይ በወንዶች ምርጥ ተጫዋች ማን ይሆናል የሚለው በጉጉት ይጠበቃል።

በዚህ ዘርፍ የማንችስተር ዩናይትዱ አማካይ ቡርኖ ፈርናንዴዝ ከፍተኛ የማሸነፍ ግምት ተሰጥቶታል። ፖርቹጋላዊው ተጫዋች ከወራት በፊት በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ 21 ግብ የሆኑ ኳሶችን በማቀበል አዲስ ታሪክ ማስመዝገቡ ይታወሳል።

አርሰናልን ከ22 ዓመት በኋላ የሊጉ አሸናፊ እንዲሆን ያስቻሉት ዴክላን ራይስ ፣ ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ እና ጋብርኤል ማጋሌሄስም ይጠበቃሉ።

የማንችስተር ሲቲዎቹ ኧርሊንግ ሃላንድ እና ራያን ቸርኪ በዕጩ ውስጥ የተካተቱ ሌሎች ተጫዋቾች ናቸው።

በወጣቶች ራያን ቸርኪ እና ኒኮ ኦራይሊ ከማንችስተር ሲቲ ፤ የአርሰናሉ ማክስ ዳውማን ፣ የቦርንማውዙ ጁኒየር ክሩፒ ፣ የሊቨርፑሉ ሪዮ ንጎሞሃ እንዲሁም የማንችስተር ዩናይትዱ ኮቢ ማይኑ በዕጩነት ቀርበዋል።

ዛሬ ምሽት በማንችስተር ኦፔራ ሃውስ በሚከናወነው ስነ ስርዓት ላይ በሴቶች እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች እጩ የሆኑ አሸናፊዎች ሽልማት ይበረከትላቸዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review