በአንደኛው ሩብ ዓመት የነዋሪዎችን የኑሮ ሁኔታና ተጠቃሚነት የለወጡ አበይት ስኬቶችን አስመዝግበናል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በአንደኛው ሩብ ዓመት የከተማችን ነዋሪዎች የጣሉብንን እምነትና የሰጡንን ኃላፊነት በታማኝነት ለመወጣት በገባነው ቃል መሠረት፣ በነዋሪዎች የኑሮ ሁኔታና ተጠቃሚነት ላይ ለውጥ ያመጡ፣ ለቀጣይ ሥራዎቻችንም መሠረት የጣሉ ውጤታማ ተግባራትን መፈጸም ችልናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከንቲባዋ የከተማ አስተዳደሩን የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ማጠቃለያ በሰጡበት ወቅት በ1ኛ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ዘርዝረዋል፡፡

የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትም፡-

1. አራት ትላልቅ የመኪና ማቆሚያና ተርሚናል ማዕከላት ተገንብተው አግልግሎት መስጠት ጀምረዋል

2. አዳዲስ መንገዶች፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን ተገንብተዋል

3. ቤቶች ተገንብተዋል

4. የውሃ ማስወገጃና የፍሳሽ መስመሮች ተገንብተዋል

5. የጎርፍ አደጋ መከላከያዎች ተሰርተዋል

6. ለ68 ሺህ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል

7. ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና ለመቀነስ የማዕድ ማጋራት ሥራዎች ተሰርተዋል

8. በሰባት የገበያ ማዕከላት ሰፊ የምርት አቅርቦት ወደ ከተማችን እንዲገባ ተደርጓል

9. የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ደረጃ ማሳደግ ተችሏል።

10. የቤት ችግር ያለባቸው እና የልማት ተነሺዎችን ንጹህ እንዲሁም የዜጎችን ክብር የሚጠብቁ ቤቶች እንዲያገኙ ተደርጓል

11. ሰላሳ ስምንት (38) የትምህርት ፕሮጀክቶች ተገንብተው ወደ ስራ ገብተዋል

12. በጤና ዘርፍ ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት ተችሏል

13. ሃያ ሶስት(23) አገልግሎቶችን ወደ መሶብ የአንድ ማእከል ዲጅታል መንግስት አገልግሎት እንዲገቡ ተደርጓል

14. ከተማችን ለህፃናት ምቹ ለማድረግ በተሰራው ስራ መጫወቻዎች ከ6 ሺህ 70 በላይ፥ የህፃናት ማቆያ 1 ሺህ 200 አድርሰናል

15. የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራዎች ተከናውነዋል

16. በቱሪዝም፣ በሰላምና ፀጥታ፣ በመብራት መሰረተ ልማት፣ በጽዳት ከፍተኛ ውጤት እንደተመዘገበ መግለፃቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review