AMN-ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም

ሊቨርፑል በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ ሁለተኛ ዙር መርሃግብር ከሜዳው ውጪ ላስክን 6ለ3 ሲያሸንፍ አዲስ ፈራሚው ብራድሊ ባርኮላ ሀትሪክ መስራት ችሏል።
ፈረንሳዊው አጥቂ ከፓሪሰን ዠርማ ሊቨርፑልን ከተቀላቀለ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ኳስ እና መረብን አገናኝቷል።
የቀዮቹን ተጨማሪ ግቦች ሮናልድ አራሆ ፣ ጀርሚ ፍሪምፖንግ እና ልዊስ ኩማስ አስቆጥረዋል። ለኦስትሪያው ክለብ ላስክ ፍሎሪያን ፍሌቸር ሁለት ግብ ሲያስቆጥር ሮበርት ሉቢቺች ቀሪውን ግብ አስመዝግቧል።
በመጀመሪያ ጨዋታው አትሌቲኮ ማድሪድን ያሸነፈው ሊቨርፑል ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አሳክቷል።
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ፋይኖርድ ኮሞን 3ለ2 አሸንፏል። ጊቫይ ዜቺል ፣ አኒስ ሀጅ ሙሳ እንዲሁም ሮበርት ሳንቼዝ እራሱ ላይ ያስቆጠረው ግብ የኔዘርላንድሱን ክለብ ባለድል አድርገዋል።
በሴስክ ፋብሪጋዝ ለሚመራው ኮሞ አሳኔ ዲአኦ እና አናስታሲዮስ ዱቪካስ ልዩነት መፍጠር ያልቻሉ ሁለቱን ግቦች አስቆጥረዋል።
በሸዋንግዛው ግርማ