AMN – ጥቅምት 7/2019 ዓ.ም

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፣የውስጥ ጥንካሬና የኢኮኖሚ ኃይል ምንጭ፤ ለኢንዱስትሪ መስፋፋት፣ ለምርት ዕድገት እና ለከተሞች ልማት ያለምንም መቆራረጥ አነስተኛ ዋጋ ያለው ኤሌክትሪክ ያቀርባል።

ኃይልን ለጎረቤት ሀገራት በመሸጥ የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘቱም በላይ የቀጣናውን የኢኮኖሚ ትስስር ያጠናክራል።
በገዛ አቅም ታላላቅ ፕሮጀክቶችን መገንባት እንደሚቻል ለአፍሪካውያን ትልቅ የስነ-ልቦና ስኬት ማሳያ ሆኗል።
ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ የየብስ እሰረኛ መሆኗ ትልቅ ስትራቴጂካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስጋት ሆኖ ቆይቷል።
ኢትዮጵያ የራሷ ባህር በር ቢኖራትና ከወደብ ጥገኝነት ብትላቀቅ ለወደብ ኪራይና ሎጅስቲክስ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ በማዳን የማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋትን ማረጋገጥ ያስችላታል።
ግድቡ የሀገር ውስጥ አቅምን በመገንባት የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን ያመነጫል ፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆኗ ደግሞ ያንን ምርት በፍጥነትና በዝቅተኛ ወጪ ወደ ዓለም ገበያ ያደርሳል።

ኢትዮጵያ ጥገኝነት ወጥታ በቀይ ባህርና በኤደን ባሕረ-ሰላጤ የንግድ መስመሮች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲኖራት በማድረግ የአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ ሞተር እንድትሆን ያደርጋታል።
ከግድቡ ወደ ወደቡ የሚደረገው ጉዞ የኢትዮጵያን የወደፊት የልማትና የጂኦ-ፖለቲካ አቅጣጫ የሚጠቁም ታሪካዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡

ግድቡ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሞተርና የኃይል ምንጭ ሲሆን ፤ ወደቡ ደግሞ የምርቶቿ መውጫና የብልጽግናዋ በረከት ማጋሪያ ድልድይ ይሆናል።
በፍሬሕይወት ብርሃኑ