የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከ22 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች

You are currently viewing የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከ22 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች

AMN ኅዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም

ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪ የደረጃ ጨዋታ ኢትዮጵያ ኬንያን አሸንፋለች።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተከናወነው ጨዋታ ኢትዮጵያ በዳዊት ካሳው ግብ 3ለ0 ማሸነፍ ችላለች።

ዳዊት ካሳው ፣ ቢንያም አብርሃ እና ብሩክ እይላቸው የኢትዮጵያን የድል ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

ዳዊት ካሳው በውድድሩ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ ሰባት ከፍ አድርጓል።

ኢትዮጵያ ማሸነፏን ተከትሎ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያን ተከትላ ሞሮኮ በምታዘጋጀው የ2026ቱ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ መሆኗን አረጋግጣለች።

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ሲያገኝ ከ22 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review