የብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማህበራት የፋይናንስ ፍላጎትን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ ነው

AMN- ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም

የብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማህበራት የዜጎችን የቁጠባ ባህል በማዳበር እና የፋይናንስ ፍላጎትን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ተመላከተ።

ተደራሽ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር 9ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል፡፡

በዚሁ ወቅት የማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ታመነ፤የብድርና ቁጠባ ማህበሩ የካፒታል አቅሙን በማሳደግ ለአባላቱ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ብድር መስጠቱን አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ 33 ቅርንጫፎች እንዳሉት እና የማህበሩ አባላትም ከ2 ሺህ 700 በላይ መድረሱን ገልጸዋል፡፡

የብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማህበራት የዜጎችን የቁጠባ ባህል በማዳበርና የፋይናንስ ፍላጎት ተደራሽ በማድረግ ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫዎቱ እንደሚገኙም ተገልጿል።

ተደራሽ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር በአዋጅ 985/2009 በሀምሌ 2/2009 በ24 መስራች አባላት እና በ24 ሺህ ብር ካፒታል የተቋቋመ የህብረት ስራ ማህበር ነው፡፡

በይታያል አጥናፉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review