ማንችስተር ዩናይትድ ዌስትሃም ዩናይትድን ይገጥማል

You are currently viewing ማንችስተር ዩናይትድ ዌስትሃም ዩናይትድን ይገጥማል

AMN ኅዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም

የ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መርሃግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከዌስትሃም ዩናይትድ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።

ወጥ ብቃት ማሳየት ያልቻለው ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ክሪስታል ፓላስን በመርታት ከአስደንጋጩ የኤቨርተን ሽንፈት አገግሟል። ኑኖ ስፕሪቶ ሳንቶን ከሾመ በኋላ መጠነኛ መሻሻል ያሳየው ዌስትሃም በሳምንቱ መጨረሻ በሊቨርፑል ተሸንፏል።

ዩናይትድ ለዛሬው ጨዋታ ማቴኡስ ኩኝሃን መልሶ ያገኛል። ሀሪ ማጓየር እና ቤንጃሚን ሼሽኮ ለጨዋታው አይደርሱም። አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከጨዋታው በፊት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ሁለት ተጫዋቾች ከስብስቡ ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል።

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ የተጫዋቾችን ስም ግን ከመጥቀስ ተቆጥቧል። ዌስትሃም ዩናይትድ ባለፈው ዓመት በሜዳው እንዲሁም ዛሬ ምሽት በሚጫወትበት ኦልድትራፎርድ ላይ ማንችስተር ዩናይትድን ማሸነፉ ይታወሳል።

የዛሬው ተጠባቂ ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ይጀምራል። ማንችስተር ዩናይትድ ድል ከቀናው ደረጃውን ወደ አምስተኛ ከፍ ማድረግ ይችላል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review