የጤና ቱሪዝም አሁን ከደረሰበት ደረጃ ይበልጥ በማጠናከር የከተማዋን ስማርት ሲቲ የማረጋገጥ ጉዞ እዉን የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም – የአዲስ አበባ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ

You are currently viewing የጤና ቱሪዝም አሁን ከደረሰበት ደረጃ ይበልጥ በማጠናከር የከተማዋን ስማርት ሲቲ የማረጋገጥ ጉዞ እዉን የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም – የአዲስ አበባ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ
  • Post category:ጤና

AMN ታኅሣሥ 15/2018 ዓ.ም

የጤና ቱሪዝም አሁን ከደረሰበት ደረጃ ይበልጥ በማጠናከር የከተማዋን ስማርት ሲቲ የማረጋገጥ ጉዞ እዉን የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አለመሆኑ በከተማዋ የታዩ ለዉጦች በራሳቸዉ ምስክሮች ናቸዉ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ገለጸ፡፡

የከተማዋን ስማርት ሲቲነት የሚያረጋግጡ የጤና ቱሪዝም ጉዞ እዉነታዎች አዲስ አበባ ከተማን የጤና ቱሪዝም መዳረሻ በማድረግ ጤናማ እና አምራች ትውልድ እንዲገነባ፣ እንዲያበለፅጋት እና ልዕልናዋን እንዲያስጠብቅላት በሚያስች ፅኑ ተግባር፣ የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ጤና ቢሮ ጋር በመቀናጀት እና ህዝብን በማሳተፍ በዘርፉ አስደማሚ ስራዎች እየሰራ ይገኛል፡፡

በመዲናዋ በሁሉም ክፍለ-ከተሞች ጭምር ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት ጋር እኩል ደረጃ ያላቸው ጤና ጣቢያዎች በዉስጥ አቅም ከፍተኛ በጀት በመመደብ በዘመናዊ የህክምና መሳሪያ እና ሙያዊ ብቃት ባላቸዉ ባለሙያዎች ጭምር እንዲደራጁ በማድረግ በተሻለ የጥራት ደረጃ ተመርቀዉ በቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ ነዉ፡፡

በተጨማሪም የነባር ሆስፒታሎችን ደረጃ ከማሳደግ ባለፈ፣ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ሊሆኑ የሚችሉ ዘመናዊ አዳዲስ ሆስፒታሎችን ግንባታ በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ የጤና አገልግሎትን በማሳለጥ ረገድ ረጅም እርቀት መጓዝ ተችሏል።

በአሁኑ ወቅት በጤናዉ ዘርፍ ለበርካታ ዘመን የከተማዋ ነዋሪዎች ላነሷቸዉ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት፤ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ በቅንነት፣በትጋት እና በታማኝነት የማገልገል ማሳያዎች ሆነዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን ስማርት ሲቲ የሚያረጋግጡ የጤና ቱሪዝምን ይበልጥ ለማሳደግ በሰጠዉ ልዩ ትኩረትም የግሉን የጤና ዘርፍ በማበረታታት፤ለጤና ተቋማት ግንባታ የሚውል የመሬት አቅርቦትን በማመቻቸ ሰፋፊ ስራዎች እየተሠሩ ሲሆን እስከ አሁን በመዲናችን ያስመረቅናቸዉን የጤና ተቋማት እየተገለገልንባቸዉ መጠበቅና መንከባከብ የስልጡን ማህበረሰብ አንዱ መገለጫ ነዉ፡፡

የጤና ቱሪዝም አሁን ከደረሰበት ደረጃ ይበልጥ በማጠናከር የከተማዋን ስማርት ሲቲ የማረጋገጥ ጉዞ እዉን የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አለመሆኑ በከተማዋ የታዩ ለዉጦች በራሳቸዉ ምስክሮች ናቸዉ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review