መንግስት ለአምራች ኢንደስትሪ ዘርፍ የሚያደርገው ድጋፍ የማምረት አቅም እንዲያድግ አድርጓል

You are currently viewing መንግስት ለአምራች ኢንደስትሪ ዘርፍ የሚያደርገው ድጋፍ የማምረት አቅም እንዲያድግ አድርጓል

AMN — መጋቢት 18/2018 ዓ.ም

ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የተወጣጣ የጋዜጠኞች በአምራች ኢንደስትሪው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛል።

በአምራች ኢንደስትሪ የተሰማሩ አካላት ለጋዜጠኞቹ እንደተናገሩት መንግስት በአምራች ኢንደስትሪው ዘርፍ የነበሩ ማነቆዎችን በመፍታት ለዘርፉ እያደረገው ያለው ድጋፍና ክትትል ምርታቸውን ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፈው ለውጪ ገበያ የማቅረብ አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

በዚህም ከገቢ በሻገር የኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የንግድ ስርአት ውድድር ውስጥ እንድትገባ ማድረግ ስለመቻሉ አስረድተዋል።

ከጥሬ ዕቃ ጀምሮ ከውጪ የሚገቡ የፋብሪካ ግብአቶችን በሐገር ውስጥ በማምረት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬን ከማዳን አልፈው የወጪ ንግድ ገቢ ማሳደግ ስለመቻላቸው ገልፀዋል።

ይህም ከአርሶ አደሩ ጀምሮ በየደረጃው ያሉ ተዋናዮችን ተጠቃሚ ስለማድረጉ ገልጸዋል።

የአምራች ኢንደስትሪው ዘርፍ መነቃቃት የስራ እድል ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው የስራ ዕድል ተጠቃሚ ወጣትቶች ተናግረዋል ።

በተለይ ፋብሪካዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የፈጠሩት ትስስር ተመራቂ ተማሪዎች በተመረቁበት የትምህርት ዘርፍ ስራ እንዲያገኙ ሰፊ ዕድልን ከመፍጠር ባሻገር በሙያ ሽግግር በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙም በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ገልጸዋል።

በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review