AMN ግንቦት 4/2018 ዓ.ም
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአሜሪካው አቻቸው ማርኮ ሩቢዮ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አካሄዱ።
በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን ዘመናትን የተሻገረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ትኩረት አድርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የሰላም እና የደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ምክክር አድርገዋል።
ሁለቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ባለው ጠንካራ የትብብር መሠረት ላይ በመነሳት ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፤ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማሳደግ፤ እና በጋራ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ ለመሥራት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ይህ ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡