“የብድር የዕዳ ሽግሽግ ድርድሩ ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ እየተጠናቀቀ ነው” — አቶ አህመድ ሽዴ

You are currently viewing “የብድር የዕዳ ሽግሽግ ድርድሩ ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ እየተጠናቀቀ ነው” — አቶ አህመድ ሽዴ

AMN ሰኔ 4/ 2018 ዓ.ም

በቡድን 20 (G-20) ሀገራት ውሳኔ የተሰጠውን የእዳ ሽግሽግ ዕድል በመጠቀም ከአበዳሪዎች ጋር በርካታ የዕዳ ሽግሽግ ድርድር ስምምነቶች በመጠናቀቅ ሂደት ላይ መሆናቸዉን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 25ኛ መደበኛ ስብሰባው የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የ2019 በጀት ዓመት የበጀት መግለጫ ማብራሪያ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ከአብዛኞቹ አበዳሪዎች ጋር የሁለትዮሽ የዕዳ ሽግሽግ ስምምነቶች መፈራረም መቻላቸውን፤ እንዲሁም የዕዳ ሽግሽግ ድርድሩ በየዓመቱ ለዕዳ ክፍያ የሚውለውን የውጭ ምንዛሬ ጫና በመቀነሱ ለልማት ፋይናንስ ተጨማሪ ሀብት ለማዋል አጋዥ መሆኑን ለምክር ቤቱ አብራርተዋል፡፡

እነዚህ የዕዳ ሽግሽግ ድርድሮች ሲጠናቀቁም የኢትዮጵያን የዕዳ ጫና ስጋት ወደ መካከለኛ ደረጃ ለማውረድ የሚያስችል እንደሚሆንም አቶ አህመድ ሽዴ ጠቁመዋል፡፡

ከ2019 በጀት አመት ጠቅላላ የመደበኛ ወጪ ውስጥ 43.8 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛው ድርሻ የተደለደለው ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ዕዳ ክፍያ መሆኑን ሚኒስትሩ አያይዘው ማስረዳታቸዉን ከምክር ቤቱ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review