AMN – ሰኔ 16/2018 ዓ.ም
የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቶች እየተላለፉ ይገኛሉ።
የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲም፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለብልጽግና ፓርቲ ላስመዘገቡት ወሳኝ ድል የተሰማኝን ከልብ የመነጨ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቴን እገልፃለሁ ብለዋል።
ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ፣ ዘርፈ-ብዙ እና ጥልቅ መሠረት ያለው ግንኙነት በእጅጉ እንደምታከብርም ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ የገለፁት።

ናሬንድራ ሞዲ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት በደስታ እንደሚያስታውሱ ጠቅሰዋል።
ስትራቴጂካዊ አጋርነታችንን እና በሕዝቦቻችን መካከል ያለውን የወዳጅነት ትስስር የበለጠ ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን ሲሉም ናሬንድራ ሞዲ አረጋግጠዋል።