አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ — የኪነጥበብ ቤት

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የትውልዱን ድምፅ ለማስተጋባትና የወጣቱን የጥበብ ጥማት ለማርካት የኪነጥበብ ማዕከልነቱን እያረጋገጠ ሲሆን የተለያየ ቀለም ያላቸውን የጥበብ ዘርፎችና ታላላቅ ጠቢባንን በአንድ ጥላ ስር በመሰብሰብ ለየት ያሉ ጥበባዊ ዝግጅቶችን በማሰናዳት ላይ ነው።

ከዚህ ቀደም ኪነጥበቡን ለመደገፍና ለማሳደግ ከተለያዩ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር አብሮ ሲሰራ የቆየን ሲሆን፣ አሁንም ያንን አጋርነት ይበልጥ አጠናክሮ ቀጥሏል።

በሀገሪቱ የፊልም ኢንዱስትሪ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል የተባለለት «ውብ አዲስ» ተከታታይ ድራማ በታዋቂው የፊልም ባለሙያ ቴዎድሮስ ተሾመ አዘጋጅነት በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ለእይታ እየበቃ ይገኛል። ይህንን ስራ ልዩ የሚያደርገው አርቲስት ተስፋዬ ሲማ፣ ሸዊት ከበደ፣ ተ/ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ እና በርካታ አንጋፋ ባለሙያዎች ዳኝነት በተደረገበት መድረክ ተፈትነው ያለፉ አዳዲስ ተዋንያን የሚሳተፉበት እና የወደፊቱ የኪነጥበብ ተስፋነታቸውን የሚያረጋግጡበት ትልቅ ፕሮጀክት ነው።

በተመሳሳይ በሙዚቃ፣ በትወና እና በሰርከስ ዘርፎች አዳዲስ ተተኪዎችን ለሀገራችን ያበረከተው «አዲስ ታለንት ሾው» በመምህርት ማህሌት ሰሎሞን ፣ መምህርት ልዩ ገዙ በድምፃዊት ፀደንያ ገብረማርቆስ ፣ አሸናፊ አለም እና ተክሉ ጥላሁን እንዲሁም በሌሎች የጥበብ ቤተሰቦች ዳኝነት የብዙዎችን ተሰጥኦ ፈትኖና አብቅቶ ወደ አዲስ ከፍታ አሸጋግሯል።

ይህ ግን የመነሻ ያህል ነው! አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከቀናት በኋላ በምንቀበለው አዲሱ ዓመት የኪነጥበብ አድማሱን ይበልጥ ሰፊ የሚያደርጉ፣ ሳቢና አዳዲስ የመዝናኛ ዝግጅቶችን ይዞላችሁ ሊከሰት ተዘጋጅቷል።

በቅርብ ቀን ለተመልካች ከሚበቁት ድንቅ ስራዎቻችን መካከል፦

• በደራሲ አዳም ግዛው ተዘጋጅቶ በአርቲስት ትእግስት ግርማ አቅራቢነት የሚቀርበው «ማሰሻ ጨርቅ »፣

• በታዋቂው ኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌ አቅራቢነት የጥበብ ሰዎችን በእንግድነት የሚያቀርበው «የጥበብ ጨዋታ»፣

• ከድምፃዊ አስገኘው አሽኮ (አስጌ ዴንዳሾ) ጋር በጥበብና በጤንነት ዙሪያ የሚያጠነጥነው «እንቁዎቹ»ይጠቀሳሉ።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከታዋቂ አንጋፋ ባለሙያዎች እስከ አዲሶቹ የጥበብ አበቦች ድረስ ሁሉንም አቀፎ «የኪነጥበብ ቤት»ነቱን በተግባር እያረጋገጠ ነው።

አዲሱን ዓመት በሳቅ፣ በጨዋታና በምርጥ የጥበብ ድግሶች አብረን ልንቀበል ተዘጋጅተናል!

እናንተስ የት ናችሁ? አዲሱን ዓመት ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በመሆን ጥበብን በቤታችሁ ተጋበዙ የኪነጥበቡም ቤተሰብ ይሁኑ!

በዮሀንስ አዳነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review