AMN-ሚያዝያ 23/2018 ዓ.ም
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ከተሞች ላይ ሲደረግ የነበረው ዛይድ የበጎ አድራጎት ሩጫ በሯጮች ምድር ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ይካሄዳል፡፡ ውድድሩን አስመልክቶም በሀያት ሪጀንሲ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።
የፊታችን እሁድ መነሻና መዳረሻውን መስቀል አደባባይ የሚደረገው የደግነትና የሰብአዊነት ሩጫ የቀድሞ የዩናትድ አረብ ኤምሬት ፕሬዝዳንት ሺህ ዛይድን መልካም ተግባራት ለማስፋፋት የሚከናወን ሲሆን ከውድድር የሚገኘው ገቢ ደግሞ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ህጻናት ይሆናል ተብሏል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መክዩ ሞሐመድ ውድድሩ በኢትዮጵያ እና በዩናይትድ አረብ ኤምሬት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር መልካም አጋጣሚ እነደሆነ ተናረዋል፡፡
የውድድሩ ከፍተኛ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል ሞሐመድ ሄላል አል ካቢ ባለፉት 25 ዓመታት ጠንከራ የበጎ አድራጎት ስራን ሲሰሩ መቆየታቸውን በመጠቆም በአዲስ አበባ ላይ መዘጋጀቱ እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል፡፡
ለውድድሩ አሸናፊዎች 600 ሺህ ብር በሽልማት እንደሚበረከትም ተገልጻል፡፡ በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ በርከታ የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ዜጎችም ተገኝተዋል።
በዮናስ ሞላ