የተፋጠነው የህገ ወጡ ህወሃት ውድቀት

AMN – ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም

የህወሃት የፖለቲካ አቋምና የተከተለው አጥፊ አካሄድ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምህዳር በውጥረት ውስጥ አስሮት ቆይቷል።

ድርጅቱ ሥልጣኑን በኃይል ለማራዘምና የተፅዕኖ ፈጣሪነቱን ለማስቀጠል የነደፋቸው ስልቶች ፣ ከጊዜ ብዛት በራሱ ውስጥ ለተፈጠሩት ስንጥቆችና ውድቀቶች ዋና መነሻ ሆነዋል።

ስልቱ በሕዝቦች መካከል ፍቅርና አብሮነትን ከመፍጠር ይልቅ ፣ የሀገሪቱን ብሔር ብሔረሰቦች እርስ በእርስ በመከፋፈልና በመጠራጠር ላይ ብቻ የተመሠረተ በመሆኑ መክሸፉ አይቀሬ ነበር።

የመከፋፈል ስልቱ ሲከሽፍበትና የሕዝብ ተቃውሞ ሲበረታበት፣ ድርጅቱ የመጨረሻ አማራጭ አድርጎ ወደ ጦርነትና የጥፋት አዙሪት ገብቷል።

ጦርነትን እንደ ዋና የፖለቲካ መሣሪያ የመጠቀም አባዜው የሕዝቡን መከራ ከማባባስ ባለፈ፣ የድርጅቱን ሕልውና ሙሉ በሙሉ አደጋ ላይ ጥሎታል።

በጦርነት ላይ የተመሠረተው የአጥፊ ቡድኑ እንቅስቃሴ በራሱ በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት መካከል የማይታረቅ ክፍፍል ፈጥሯል።

የሰላምንና የልማትን በር ዘግቶ በጦርነት ላይ ብቻ ማተኮሩ፣ የሰው ሕይወት እንዲጠፋና የቁሳቁስ ውድመት እንዲከሰት በማድረጉ ሕዝቡ በህውሃት ላይ ላይ ውግዘት እያዘነበ ይገኛል።

የክልሉ ሕዝብ ከረጅም ዓመታት መራር ግጭት በኋላ እንደ ሌላው የሀገሪቱ ክፍል የሰላም፣ የልማትና የመበልፀግ ጥማቱ በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል።

ሕዝቡ ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት ለመሸጋገር ያለው ጽኑ ፍላጎት፣ ድርጅቱ በኃይል ሕዝቡን ለመግዛት የነበረውን ፍላጎት አኮስምኖታል።

የጽምዶ ስልት መክሸፉ፣ በጦርነት ላይ የተመሠረተ አጥፊ የፖለቲካ አካሄድ መከተሉ፣ የውስጥ ክፍፍል መባባሱ እና የሕዝብ እምነት ሙሉ በሙሉ ማጣቱ የሕገ ወጥ ቡድኑን ውድቀት እያፋጠኑት ይገኛሉ።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review