የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠናዎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ

You are currently viewing የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠናዎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ

AMN – ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም

የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ቀጠናዎች በፋርማሲዩቲካል እና በግብርና ማሽነሪ ማምረት ዘርፎች በጋራ የንግድ ሽርክና እንዲሰማሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻልና በግብርናው ዘርፍ ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየሰራች መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ትብብር በግብርና ማሽነሪዎችና ሰብል በማቀነባበር በኩል ይህንን ግብ ለማሳካት ትልቅ ሚና እንደሚጫወትም ነው የገለጹት።

አፍሪካ በአህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና በኩል አንድ ወጥ ገበያ እየገነባች በመሆኗ፣ በኢትዮጵያ የሚመሠረቱት እነዚህ ኩባንያዎች አጠቃላይ የአፍሪካን ገበያ ማግኘት የሚያስችል ዕድል እንደሚፈጠርላቸው አብራርተዋል።

የሁለቱን ሀገራት የንግድና የኢኮኖሚ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የክፍያ ቻናሎችን ማቃለልና ወጪያቸውን መቀነስ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የተነደፈው አዲስ የድርጊት መርሃ ግብር ግልጽ የጊዜ ገደብና ተግባራትን ያቀፈ እንዲሆን እና ስምምነቶች ወደ ተጨባጭ ውጤት ሊለወጡ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review