የአዲስ አበባን የትራንስፖርት ዘርፍ ለማዘመንና አገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ ለማድረግ ሰፊ የለውጥ ስራዎች እየተሰሩ ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የአዲስ አበባን የትራንስፖርት ዘርፍ ለማዘመንና አገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ ለማድረግ ሰፊ የለውጥ ስራዎች እየተሰሩ ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም

የመዲናዋን የትራንስፖርት አገልግሎት በጥራት፣ በብቃትና በዘመናዊ መልኩ ለማደራጀት ዘርፈ-ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት፣ የመጀመሪያዎቹን 26 ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተለወጡ አውቶብሶች ሥራ አስጀምረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ “የመዲናዋን የትራንስፖርት ችግር ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታትና አገልግሎቱን ለማዘመን አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ ጥረት እያደረግን እንገኛለን ብለዋል።

የከተማ አውቶቡሶችን ለማቅረብ ከፍተኛ በጀትና የቢሊዮኖች ድጎማ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ የህዝባችንን ፍላጎትና ተደራሽነት በብዙ እጥፍ ማሳደግ እንዳለብን በመገንዘብ በትኩረት እየሰራን ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ከንቲባዋ አክለውም፣ አዳዲስ አውቶቡሶችን ከመግዛት ባሻገር፣ ነባሮቹን የከተማ አውቶቡሶች የውስጥ አካል (ኢንጂን) ወደ ተፈጥሮ ጋዝ በመቀየር ወጪ ቆጣቢ፣ አካባቢ ጥበቃን ያከበሩና ምርታማ እንዲሆኑ ተደርጓል ብለዋል።

በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩት እነዚህ አውቶቡሶች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የትራንስፖርት ወጪና እንግልት በእጅጉ እንደሚቀንሱ ገልጸዋል።

የዚህን ስኬት እንደ መልካም ተሞክሮ በመውሰድ፣ በቀጣይም በርካታ አውቶቡሶችን ወደዚሁ የቴክኖሎጂ ስርዓት የማሸጋገር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review