AMN- ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም
የከተማዋን ነዋሪዎች ደህንነት ከአደጋ ለመጠበቅና የአደጋዎች ምላሽ አሰጣጥን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር አቅሙን እያሳደገ መምጣቱን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታቋል።
ኮሚሽኑ በፖላንድ መንግስት በተደረገ ድጋፍ በአቃቂ ቃሊቲ የተገነባውን የተግባር መለማመጃ ማእከልን አስመርቋል።
የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነዋሪዎች ደህንነት ከአደጋ ለመጠበቅና የአደጋዎች ምላሽ አሰጣጥን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር አቅሙን እያሳደገ ይገኛል፡፡
ይህንኑ ተግባሩን ይበልጥ ለማጠናከር ኮሚሽኑ ከፖላንድ ዓለም አቀፍ እርዳታ ማዕከል እና ከዓለም አቀፍ የገጠር መልሶ ግንባታ ጋር በመተባበር ለህብረተሰቡ ደህንነት ትልቅ ፋይዳ ያለውን የተግባር መለማመጃ ሲሙሌሽን ፕሮጀክት አስመርቋል፡፡
ኤ ኤም ኤን ያነጋገራቸው የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ያገኙት ስልጠና እውቀትና ክህሎት የላቀ የአደጋ ምላሽና የፈልጎ ማዳን አቅማቸውን ከማሳደጉም ባሻገር፣ የእውቀት ሽግግርም ያገኘንበት ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጥላሁን ቶላ የከተማዋን ነዋሪዎች ደህንነት ከአደጋ ለመጠበቅና የአደጋዎች ምላሽ አሰጣጥን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር አቅሙ እያሳደገ ይገኛል ብለዋል።
የፖላንድ የተራድኦ ድርጅት የተለያዩ ግብአቶችን ጨምሮ ለቅድመ አደጋ መከላከልና ለአደጋ መቆጣጠር ሠራተኞቹ አቅም የመገንባት ስራ መከናወኑን ታናግረዋል፡፡
ምክትል ኮሚሽነር ጥላሁን ቶላ ከ108 በላይ የሚሆኑ የኮሚሽኑ ባለሙያዎችን አቅም የመገንባት ስልጠና መውሰዳቸው በከተማችን ለሚከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባን እድገት የሚመጥን የእሳት አደጋ ቅድመ መከላከል ስልጠና ለኮሚሽኑ ባለሙያዎች መሰጠቱን የገለጹት በኢትዮጵያ የፖላንድ ዓለም አቀፍ የገጠር መልሶ ግንባታ ድርጅት የፕሮግራም ዳይሬክተር ወርቅነህ ንጋቴ (ዶ/ር) ይህም ተግባር ተጠናከሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ለኮሚሽኑ በአደጋ ቅነሳ፣ በአደጋ ምላሽ፣ በመልሶ ማቋቋም፣ በቴክኖሎጂና ምህንድስና ዘርፎች ይበልጥ ለመትጋት ማሰልጠኛ ማአከሉ የጎላ አስተዋፆ እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡
በመሃመድኑር አሊ