ከአዲስ አቀራረብና ውብ ገፅታ ጋር ወደ እናንተ መጥታለች
በዜና ገፆቿ

· ከእንጦጦ እስከ ቀበና የተሰራው የወንዝ ዳርቻ ልማት ወንዙን ወደ ቀደመ ተፈጥሯዊ መልኩ መመለስ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ወዝን ከከተማ ባህሪ ጋር በማዋሃድ ረገድ ያለውን አበርክቶ ዳስሳለች፤
• በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተካሄዱ ያሉ የቤት ግንባታዎች የከተማዋን ስምና ግብር ከማጣጣም እና ለነዋሪዎች ክብራቸውን የሚመጥን ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አንፃር ስላላቸው ጠቀሜታ ታስቃኛለች፤
በአንኳር ጉዳይ
• በቱሪዝም ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እና እያስገኙት ያለው ጥቅም እንዴት ያለ ነው? ስትል ባለሙያ ጠይቃለች፤
የጠዋት ፀሐይ
• ልጆች ችግኝ መትከል የሚያስገኘውን ጥቅም እንዲገነዘቡ የሚያስችል ምክር ከሌሎች አዝናኝ መረጃዎች ጋር ይዛለች፤
በመዝናኛ
• በተለያዩ የሙዚቃ ስራዎች ሽፋን ስላገኘው የቀበና ወንዝ የቀደመ እና አሁናዊ ገጽታ ዳስሳለች፤
በስፖርት
• በዓለም ዋንጫ ታሪክ ያልተጠበቀ ተአምር የሰሩ የአፍሪካ ሀገራትን ታስቃኛለች፡፡
በተጨማሪም ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ይዘት ያላቸውን ሌሎች ዘገባዎች አካትታ ቅዳሜ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ እናንተ ትደርሳለች፡፡
መልካም ንባብ
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አዲስ ልሳን ጋዜጣ፤ የትውልድ ድምፅ