AMN- ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም

ሙስና እና ብልሹ አሰራር በጊዜ እንዲገታ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን ገልጸዋል፡፡
ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን፤ሙስና እና ብልሹ አሰራር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ለመከላከል በሰፊው እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የኦዲት ፎረም ተቋቁሞ ተጠያቂነት እንዲሰፍን እየተደረገ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡
ግንጸኝነትን እና አሳታፊነትን ተግባራዊ በማድረግ የማህበረሰብ ተሳትፎ እንዲጎለብት እየተደረገ መሆኑንም ሃላፊው ገልጸዋል፡፡
ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት በተሰራው ሥራ ውጤት ተገኝቷል ያሉት አቶ አብዱልቃድር፤ ግልጸኝነትን እና አሳታፊነትን እንዲሁም ተጠያቂነትን የሚያጠናክሩ ተግባራት መከናወናቸውን ገለፀዋል፡፡
ብልሹ አሰራር በዜጎች መካከል ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዳይኖር በማድረግ የሃገርን ኢኮኖሚ ጭምር ወደ ኋላ የሚጎትት ነው፡፡
መንግስትም ሙስናን ሃገራዊ ችግር አድርጎ በመውሰድ በተቀናጀ መንገድ ለመከላከል የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የተቋማት አቅም አለመዳበር እና የህዝብ ግንዛቤ በሚፈለገው ልክ አለመጎልበቱ የጸረ ሙስና ትግሉ የሚፈለገውን ውጤት እንዳያመጣ እንቅፋት እንደሆነ በተደጋጋሚ ይገለጻል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱና አገልግሎቶች ከሙስና በጸዳ አግባብ እንዲሰጡ በትኩረት እየሰራ ሲሆን፤ ተጠያቂነትን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
በየሻምበል ምህረት