AMN- መስከረም 11/2019 ዓ.ም

ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ከፍ ያደረጉ የመስቀልና ኢሬቻ በዓላት ሐይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ የዕምነት አባቶችና ህብረተሰቡ የራሳቸውን ድርሻ ማበርከት እንዳለባቸው ተገለጸ።
በየካ ክፍለ ከተማ የአደባባይ በዓላት አከባበርና የበዓላቱ ትውፊትና እሴቶች ዙሪያ ከተለያዩ ወረዳዎችና የዕምነት ተቋማት ከተውጣጡ የእምነት አባቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ እሸቱ ለማ (ዶ/ር)፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ጠንካራ አንድነት ያላት እንድትሆን የዕምነት ተቋማትና አባቶች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
የመስቀልና ኢሬቻ በዓልን ለመታደም በርካታ እንግዶች ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ እንደሚመጡም ተናግረዋል።
በመሆኑም ከፊታችን የሚከበሩ ተላላቅ የአደባባይ በዓላት ለቱሪዝም ፋይዳ ለማዋል እና ሐይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸው ጠብቀው እንዲከበሩ ከእምነት አባቶችና ከህብረሰቡ የላቀ ድርሻ ይጠበቃል ብለዋል።
በዓላቱ በዓለም ላይ ጎልተው እንዲታዩ እና ወጣቶች ተገንዝበው ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም የዕምነት አባቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በዓለሙ ኢላላ