AMN – ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስነስርዓት ላይ ያደረጉትን ንግግር አስመልክቶ የቀረበ የድጋፍ ሞሽን አዳምጧል።

የድጋፍ ማሽኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ፍቃዱ ተሰማ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
የመክፈቻ ንግግሩ በተለይም በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን በ2019 በጀት ዓመት መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ሊያከናውናቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

የድጋፍ ሞሽኑም በምክር ቤት አባል ድጋፍ ያገኘ ሲሆን፣ በቀጣይ ሞሽኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እንደሚጸድቅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አህመድ ሽዴ መናገራቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።